ኢየሱስን የሕይወታችሁ ጌታ አድርጉት።

“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናል።”

ሮሜ 10፥9–10

“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”

ኤፌሶን 2፥8-9

ዛሬ፣ እንዲህ በመጸለይ ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወታችሁ ጌታ እንድታደርጉት እንጋብዛችኋለን።

አቤቱ ጌታ ሆይ ፣ እኔ በሙሉ ልቤ በሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ፡፡ ስለኔ ኃጢኣቴ እንደሞተ፡ እንደተቀበረ፡ በ’ሥስተኛው ቀንም እንደተነሳ ዛሬም በህይወት እንዳለ አምናለሁ፡፡ አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበልሃለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ መሆኑን በአፌ እመሰክራለሁ። እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልቤ አምናለው። በእርሱ እና በስሙ የዘላለም ሕይወት አለኝ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እቀበልሃለሁ። ከዚህ ቀን ጀምሮ በልቤ ውስጥ የዘላለም ሕይወትን በእምነት ተቀብያለሁ። ጌታ ሆይ ስለ የነፍሴን ማዳን አመሰግንሃለሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ፡፡ ሃሌ ሉያ!

“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”

2ኛ ቆሮ 5፥17

ይህን ጸሎት ከጸለያችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ናቹ፡፡ ሃሌ ሉያ!!!

ከታች ያለውን ቅጽ በመሙላት፣ ቤተክርስቲያናችንን በመጎብኘት ወይም በተዘጋጀው ስልክ ቁጥር እንድታገኙን እንጋብዛለን። ቅጹን መሙላት በጌታችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና እውቀት እያደገ እና ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር መጽሐፍ ቅዱስን በምታጠናበት ጊዜ ከእርስዎ ጋር እንድንገናኝ እና እንድንደግፍ ያስችለናል።


📍

አድራሻ፡ መስቀል ፍላወር ከናዝራ ሆቴል ጀርባ ከዚግዛግ ሆቴል ማዶ አዲስ አበባ

☎️

ለበለጠ መረጃ፡ +251 901122180፡ +251 976054800 ይደውሉ!